የቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆነ

ሀያላን የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች የሚፋለሙበት ተወዳጁ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ቀጣይ ጨዋታዎች ድልድል ተካሂዷል፡፡

የዓምናው የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ከዴንማርኩ ኮፐንሀገን ጋር ተደልድሏል፡፡

እንዲሁም ምድቡን በበላይነት ያጠኛቀቀው አርሰናል ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር ሲደለደል ናፖሊ ከባርሴሎና፣ ፒኤስጂ ከሪያል ሶሴዳድ፣ የአምናው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ፒኤስቪ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ላዚዮ ከባየር ሙኒክ እንዲሁም ላይፕዝሽ ከሪያል ማድሪድ እንደሚጫወቱ ተገልጿል፡፡

ናፖሊ ከባርሴሎና፣ ላይፕዝሽ ከሪያል ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ከባድ ፉክክር ሊደረግባቸው የሚችሉ ጨዋታዎች እንደሚሆኑ ተጠብቋል፡፡

አራት የስፔን ክለቦች ወደ 16 ውስጥ በመግባት የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ያለፉ ሲሆን ጣልያን ሶስት እንግሊዝ እና ጀርመን ሁለት ሁለት ክለቦቻቸው ይሳተፋሉ፡፡

የ2022/23 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የጣልያኑ ኢንተር ሚላን እና የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ለፍጻሜ አልፈው ሲቲ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የቻምፒዮንስ ሊግ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ውድድር ከአንድ ወር እረፍት በኋል ከየካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መካሄድ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

ሌላኛው የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድልን ይፋ ያደረገ ሲሆን ፊኖርድ ከሮማ፣ ኤሲ ሚላን ከስታድ ሬኒስ፣ ሌንስ ከፍራይቡርግ፣ ያንግ ቦይስ ከስፖርቲንግ ሊስበን፣ ቤኔፊካ ከቱሉስ፣ ብራጋ ከካራባህ፣ ጋላታሳራይ ከስፓርታ ፕራግ እና ሻክታር ዶኔስክ ከማርሴይ ጋር ተደልድለዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *