ፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ የዓመቱ ምርጡ ፕሮፌሰር ተባሉ

ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ዓለም አቀፉ የፕሮፌሰሮች ማህበር ኢትዮጵያዊውን ፕሮፌሰር ሙላቱ ተሰማ የዓመቱ ምርጥ ምሁር በሚል እውቅና ሰጥቷል፡፡

ማህበሩ በየዓመቱ በመላው ዓለም ላሉ ፕሮፌሰሮች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን የ2023 ዓመት እውቅናን ለኢትዮጵያዊው የሂሳብ ፕሮፌሰር ማድረጉ ተገልጿል፡፡

በመላው ዓለም ያሉ ፕሮፌሰሮች ባስገኙት ስኬት፣ የትምህርት አመራር፣ በሙያው ላይ ባደረጉት ቆይታ እና ሌሎች ጥረቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በየዓመቱ በዚህ ማህበር ይሸለማሉ፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መረጃ መሰረት ፕሮፌሰር ሙላቱ ተሰማ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

የሶስተኛ ድግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካው ኬንት ስቴት ዩንቨርሲቲ እንዳገኙ የተገለጸው ፕሮፌሰር ሙላቱ ላለፉት 28 ዓመታት ደግሞ በዚያው በአሜሪካ ሳቫና ስቴት ዩንቨርሲቲ በማስተማር ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሮፌሰር ሙላቱ ከአራት ዓመት በፊት በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሽልማት ተበርከቶላቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምሁሩ በፈረንጆቹ 2020 ላይ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ሽልማት የተበረከተላቸው ለቀጣዩ ትውልድ ሳይንስ እና ሂሳብ ትምህረቶች ባበረከቱት አስተዋጽኦ ምክንያት ነበር፡፡

ፕሮፌሰር ሙላቱ ወጣት የሳይንስ እና ሒሳብ ተማሪዎችን በማማከር፣ በማሰልጠን እና በማብቃት ለዓመታት መስራታቸው ለበርካታ ሽልማቶች እንዳበቃቸው ተገልጿል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *