ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ሰባተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል፡፡

ዛሬ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት አማኔ በሪሶ አትሌት ጎቲቶም ገብረ ስላሴ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡

ሞሮካዊቷ አትሌት ፋጥማ ጋርዳዲ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ልታገኝባቸው የምትችልባቸው ቀሪ ውድድሮች ያሉ ሲሆን አሁን ላይ በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እና በሁለት ነሀስ በደምሩ በስምንት ሜዳሊያዎች ከዓለም በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

አሜሪካ በስምንት የወርቅ፣ ስፔን በአራት ወርቅ እንዲሁም ጃማይካ በሶስት የወርቅ ሜዳሊያ ከአንደኛ እስከ ሶተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬ እና ነገ በሚካሄዱ የወንዶች ማራቶን፣ በሴቶች እና ወንዶች አምስት ሺህ ሜትር ውድድሮች ላይ የምትሳተፍ ሲሆን ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን እንደምታገኝ ትጠበቃለች፡፡

ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር እና ማራቶን ውድድሮች ወርቅ ስታገኝ፣ በ10 ሺህ፣ በሶስት ሺህ መሰናክል፣ በ1500 ሜትር ሴቶች እና በማራቶን ውድድሮች የብር ሜዳሊያዎችን ቀሪዎቹ ሁለት የነሀስ ሜዳሊያዎች ደግሞ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች እና ሴቶች የተገኙ ናቸው፡፡

19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ነገ ምሽት የሚጠናቀቅ ሲሆን ከዚህ በፊት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ቀዳሚ የነበሩት ቻይና፣ ኬንያ፣ ብራዚል እና ሌሎችም ሀገራት ዘንድሮ ድል እየቀናቸው አይደለም፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *