ወደ አሜሪካ ካቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሁለት ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ወደ አሜሪካ አቅንቶ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርጎ ተመልሷል።

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሜሪካ ቆይታን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በአሜሪካ ቆይታው አላማውን እንዳሳካ የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።

የዲሲ ዩናይትድ ድርሻ ያላቸው አቶ እዮብ ማሞ ከፌዴሬሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ ላይ በቅርቡ ከስምምነት እንደሚደርሱም አቶ ባህሩ ገልጸዋል።

ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቅርቡ ወደ አሜሪካ በማቅናት ስምምነቱን ይፈፅማሉም ብለዋል።

ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የሚደረገው ስምምነት ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች በዲሲ ዩናይትድ የመጫወት እድልን እንዲያገኙ እንደሚያስችል አቶ ባህሩ አክለዋል።

ይሁንና የቡድኑ የትጥቅ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አውግቼ እና የፊዚዮቴራፒ ባለሙያው ሽመልስ ደሳለኝ ከሆቴላቸው በመጥፋታቸው ከቡድኑ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንዳልተመለሱ ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *