በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ጋዜጠኞች የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቆ ሆኖ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ተወሰነ

አራት የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረጓል።

በሽብር ወንጀል የተከሰሱ አራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ሌሎች 19 ተከሳሾች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ፤ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ።

የተከሳሾችን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ያወጣውን መግለጫ በድረ ገጻቸው የጫኑ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን እንዲያወርዱም ፍርድ ቤቱ አዝዟል።

ይህን ትዕዛዝ የሰጠው ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ነው።

ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ ትዕዛዞችን በሰጠበት ቅጽበት ተከሳሾች በጭብጨባ የታጀበ መፈክር አሰምተዋል።

የተከሳሾቹ መፈክር እና ጭብጨባ፤ የችሎት ውሎ ተጠናቅቆ ታዳሚዎች ከአዳራሽ ከወጡ በኋላም አላቋረጠም ነበር ተብሏል።

በተከሳሾች ጭብጨባ የተጠናቀቀው ችሎት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው፤ ጠበቆች ባቀረቡት የተከሳሾች የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት እና ከዚህ በፊት የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈጻጸም ለመከታተል ነበር።

የተከሳሾችን የዋስትና መብት በተመለከተ ከ20 ቀናት በፊት በነበረ የችሎት ውሎ በተደረገ ክርክር፤ ጠበቆች የደንበኞቻቸው የዋስትና ጉዳይ ሊታይ የሚገባው “የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ እና በህገ መንግስቱ እንጂ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ አይደለም” ሲሉ ተከራክረዋል።

ይሁንና ችሎቱ የቀረበለትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ታስረው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *