ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ቀዳሚ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

የአልናስር አጥቂ የሆነው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልድ የ2023 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ የአምስት ጊዜ ባሎንዶር ተሸላሚው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በተያዘው ዓመት ብቻ 136 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል።

የዓለም ዋንጫ አሸናፊው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ በ2022 ዓመት 130 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ተከፍሎታል።

ክርስቲያኖ ካገኘው የ136 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዶላሩን ከሜዳ ውጪ ማለትም ከማስታወቂያ እና ስፖንሰር ስራዎች ማግኘቱ ተገልጿል።

በማንችስተር ዩናይትድን ባለ መግባባት ወደ ሳውዲ አረቢያው አልናስር ያመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደመወዙ እጥፍ እንዳደገለትም ተገልጿል።

በአጠቃላይ በስፖርቱ ዘርፍ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዱረጃን ይዘዋል።

የቅርጫት ኳስ ኮኮቡ ለቦርን 119 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ቦክሰኛው ካኒሎ አልቫሬዝ ደግሞ በ110 ሚሊዮን ዶላር በሚከፈላቸው የገንዘብ መጠን አራተኛ እና አምስተኛን የያዙ ስፖርተኞች ናቸው።

አሜሪካዊቷ እና የቴንስ ስፖርት ኮኮቧ ሴሪና ዊሊያምስ በ45 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት በሴቶች ዘርፍ ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ተብላለች።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *