ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የነበረ ሩሲያዊ ዜጋ ህይወቱ አለፈ

ግለሰቡ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማን በመጎብኘት ላይ እያለ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡

የ55 ዓመት እድሜ እንዳለው የተገለጸው ይህ ሩሲያዊ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ሀይቅ ላይ በመዋኘት ላይ እያሉ ህይወቱ አልፏል ተብሏል፡፡

በቢሾፍቱ ኩርፊቱ ሀይቅ በመዝናናት ላይ ከነበሩት የዉጭ ሀገር ዜጎች መካከል አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለዉ የ 55 ዓመት ህይወቱ ማለፉን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት ግለሰቡን ለሞት ያበቃዉ በኩሪፍቱ ሀይቅ 150 ሜትር ጥልቀት ባለው ኩሪፍቱ ሀይቅ ዘልቆ በመዋኘት ላይ ሳለ ህይወቱ ማለፉን ተገልጿል፡፡

ግለሰቡ ባሳለፍነው እሁድ ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ለመዋኘት ወደ ሀይቁ ውስጠኛው ክፍል ከገባ በኋላ ሳይመለስ ቀርቷል ተብሏል፡፡

የሩሲያዊውን ዜጋ አስከሬን ለማውጣት ብዙ ሙከራዎች ከተደረጉ በኋላ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ዋናተኞች ከሁለት ሰዓት ፍለጋ በኋላ አስከሬኑን መገኘቱ ተገልጿል፡፡

ቢሾፍቱ ከተማ በውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የምትታወቅ ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡

በኢትዮጵያ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ብዙም ያልተለመደ ሲሆን የሩሲያዊው ዜጋ መሞቱ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *