የቲንክ ያንግ ኮዲንግ ስኩል ስልጠና በድጋሜ ሊጀምር እንደሆነ ተገለጸ

ቲንክ ያንግ (ThinkYoung) እና ቦይንግ (Boeing) ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 20ኛው የThinYoung Codeing School ምዝገባ መጀመሩን አስታውቀዋል።

መርሃ ግብሩ ከሀምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2015 ዓ. ም የሚካሄድ ሲሆን እድሜያቸው ከ9-18 ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነፃ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ትምህርት ይሰጣል ተብሏል።

የቲንክ ያንግ ኮዲንግ ትምህርት ቤት ሥርዓተ ትምህርት በባለሙያዎች የተመቻቹ ሮቦቲክስ እና ሮቦቲከስን  ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን የሚሽፍን ይሆናል።

በተጨማሪም የቦይንግ ተወካዮች በአቪዬሽን እና በሌሎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ መስኮች ተነሳሽነትን ለመፍጠር ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች እንደሚያካፍሉ ተገልጿል።

እንዲህ ባለው የቲንክ ያንግ እና በቦይንግ አጋርነት በመሰል ኮዲንግ ትምህርት ላይ በተሳተፉ ከ1,300 በላይ ወጣቶች ህይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድረ ሲሆን በቀደሙት ዙሮች ውስጥ ከ 60% በላይ ተሳታፊዎች ሴቶች ነበሩ።

ፕሮግራሙ ኋላቀር አስተሳሰብን በመስበር  ሴቶች ልጆች አርአያ እንዲሆኑ እና ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር ቀደም ብለው መተዋወቅ እንዲችሉ የሚያግዝ ከባቢንም ይፈጥራል ተብላል።

ይህ የ ThinkYoung code School  መረሀ ግብር ኢትዮጵያን 70% የሚሆነውን ህዝቧን አስፈላጊ የዲጂታል ክህሎት እነዲኖራቸው ለማስቻል የያዘችውን እቅድ ለመደገፍ ያለመ ነው።

መርሃ ግብሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን በማብቃት በወደፊት ስራቸው ስኬታማ ለመሆን እንዲዘጋጁ እና ለአገሪቱ የቴክኖሎጂ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ያግዛል።

በመሆኑም እድሜያቸው ከ9-18 ዓመት የሆኑ ሁሉ ከስር ባለው ሊንክ ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

https://www.thinkyoungcodingschool.com/

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *