የለንደን ማራቶች ከደቂቃዎች በፊት የሁለቱም ጾታ ተዉዳዳሪዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።
በዚህም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና በዜግነት ሆላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን አንደኛ ወጥታለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሲፋን ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ37 ማይክሮ ሰከንድ አጠናቃለች።
ኢትዮጵያዊቷ መገርቱ አለሙ ሁለተኛ ጀፕችርችር ፒሬዝ ከኬንያ ሶስተኛ ወጥተዋል።
በርቀቱ ተጠብቃ የነበረችው አልማዝ አያና ውድድሯን በሰባተኝነት አጠናቃለች።
በወንዶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኬንያዊው ኬልቪን ኪፕቱም በ2 ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ25 ማክሮ ሰከንድ አንደኛ ሲሆን ሌላኛው ኬንያዊ ጂዎፍሪ ካምዎሮር ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ደግሞ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።
ልኡል ገብረስላሴ እና ሰይፉ ቱራ ደግሞ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ የኢትዮጵያ አትሌቶች ናቸው።
በውድድሩ ተጠብቀው የነበሩት እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ዘጠነኛ እንዲሁም ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ በውድድሩ ተጠብቆ የነበረ ቡሆንም ድል አልቀናውም።