እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 በዋለው ችሎት ነው፡፡ 

በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል።

ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፤ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ” መሆኑን ገልጿል። 

በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት አቶ ኩምሳ ቶላ ይገኙበታል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *