በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ።
” ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ” የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው።
ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ እያለ በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ማዕበል የመስጠም አደጋው አጋጥማል።
በአደጋው የጀልባውን ሹፌር ጨምሮ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
አደጋው መከሰቱ እንደታወቀ የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ጥረት ቢደረግም በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት አልተሳካም።
ከአደጋው መድረስ በኋላ ከአርባ ምንጭ ከተማ በመጡ ዋናተኞች ጭምር ሕይወት ለማዳን ቢሞከርም በሰዓቱ የነበረው ማዕበል አላስቻለም ተብሏል።
በጫሞ ሐይቅ ላይ የነበረው ማዕበል ዛሬ ጠዋት ጋብ ማለቱን ተከትሎም ፤ የሟቾችን አስክሬን ለማግኘት በተካሄደ ፍለጋ፤ የሁለት ሰዎች አስክሬን በሐይቁ ዳርቻ ማግኘት ተችሏል።
ህይወታቸው ያለፈ ቀሪ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት ፍለጋው አሁንም መቀጠሉን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
በኢትዮጵያ በሀይቆች ላይ የማዕበል አደጋ አጋጥሞ የማያውቅ ሲሆን አሁን በደቡባዊ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ ዙሪያ ባለው ጫሞ ሀይቅ ላይ አጋጥሟል።