ከ10 ዓመት በፊት ለተፈጸመ ታክስ ማጭበርበር ቅጣት እንዲጣል የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ተዘጋጀ
ማንኛውም ደረሰኝ ሳይቆርጥ የተገበያየ አካል በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርሰው የተሻሻለው የታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡
ረቂቁ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ለ10 ዓመታት ወደኋላ በመሄድ ሂሳቡን በመመርመር ወይም ሂሳብ ኦዲት በማድረግ ተጨማሪ ግብር ማስከፈልን ለገቢ ሰብሳቢው የሚፈቅድ ነው፡፡
ዛሬ ለምክር ቤቱ የቀረበው ረቂቅ የግብር አስተዳደር አዋጅ በተለይ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚደረግ ግብይት ላይ ከፍ ያለ ቅጣትን ...