Medicalawards

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ለሁለት ሐኪሞች የህይወት ዘመን ሽልማትን አበረከተ

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ለሁለት ሐኪሞች የህይወት ዘመን ሽልማትን አበረከተ

ማህበሩ 59ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሂዷል። ማህበሩ በጉባኤው ላይ በህክምና ሙያ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለሰጡ ሁለት ሐኪሞች የህይወት ዘመን ሽልማትን አበርክቷል ። ዶክተር ይርጉ ገብረህይወት በወንድ ጾታ እንዲሁም ዶክተር ተቋም ደበበ ደግሞ በሴት የህይወት ዘመን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ተሸላሚዎቹ በሕክምና ሙያቸው በአንጻራዊነት የተሻለ የሕክምና አገልግሎት እንደሰጡ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከህይወት ዘመን ሽልማት በተጨማሪ ዶክተር ትህትና ንጉሴን በሴት ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀኪም በሚል ሲሸልም ዶክተር ፈለቀ አግዋርን ደግሞ በወንድ ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀኪም ሲል ሸልሟል። አዲስ ህይወት የማገገሚያ ማዕከል ደግሞ የዓመቱ ምርጥ የጤና ተቋም በሚል ተሸልሟል። ሽልማቱን የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የኢትዮጵያ…
Read More