Graduates

ኢትዮጵያ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብሔራዊ ግዳጅ ልትጥል ነው

ኢትዮጵያ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብሔራዊ ግዳጅ ልትጥል ነው

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቋል። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል። ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል። ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል…
Read More