01
Mar
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ወንድ ልጅ ሃራሬ ውስጥ በተዘጋጀ ድግስ ላይ ንብረት አውድሟል ተብሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ። 31 ዓመቱ እንደሆነ የሚገመተው ሮበርት ሙጋቤ ጁኒዬር ሶስት ንብረት የማውደም እና ሁለት ፖሊስ የመተናኮስ ክስ ቀርቦበታል ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል። በድግሱ ላይ የመኪናዎች መስታወት ሲረግፍ አንድ የፖሊስ መኮንን ላይ ምራቅ መተፋቱ ተሰምቷል። የሙጋቤ ልጅ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎ ከደሙ ንፁሕ ነኝ ይላል። አሁን ከእሥር ተለቆ ክሱን በድርድር ለመፍታት እየጣረም እንደሆነ ተነግሯል። ፖሊስ በትዊተር ገፁ እንደገለጠው የሮበርት ሙጋቤ ልጅ ጓደኛ የሆነው ሲንዲሶ ንካታዞ ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ ነው ፖሊስ ወደ ሥፍራው ያቀናው። በድግሱ ላይ የደረሰው የንብረት ውድመት በገንዘብ ሲሰላ 12 ሺህ ዶላር አካባቢ ሊደርስ እንደሚችል ፖሊስ…