01
Mar
በጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የትዊተር አካውንት ህገወጥ የጦር መሳርያዎች እና ጥይቶች በባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የፓትርያርኩ ፅ/ቤት አመራር በሆኑት በአቶ አቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ ተገኝተዋል በማለት ሶስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ይህ የትዊተር ፖስት በፖሊስ ፍተሻ ከአቡነ አብርሃም የመኖርያ ቤት ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ መሳርያዎች ከ235 ጥይት ጋር ተገኝቷል የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አጋርቶ ነበር። ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የትዊተር ፖስት ወደ አንድ መቶ ያህል ጊዜ መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተመልክተውታል። ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ተመልክቶ መረጃውን እንደማይደግፍ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል። በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን…