01
Mar
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ በትግራይ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ከቆመ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀለ ገቡ። ፓትሪያርኩ ወደ ትግራይ ያቀኑት ከቀናት በፊት በሞት በተለዩት የመቀለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጻጻስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ዳግማዊ የሽኝት ሥነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው። አቡነ ማቲያስ ለሁለት ዓመት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ወደ ትግራይ ሲያመሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ፓትሪያርኩ በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ በይፋ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ሰላም እንዲወርድም በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። ነገር ግን በትግራይ ክልል ያሉ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በጦርነቱ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ባሉ ምዕመናን…