አይሾው ስፒድ የተሰኘው ተጽዕኖ ፈጣሪ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ከ240 ሺህ በላይ ሰብስክራይበር ማግኘቱ ተገለጸ

አሜሪካዊው ተጽዕኖ ፈጣሪ ዩቲዩበሩ I show speed በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የአንድ ቀን ቆይታ አድርጓል።

ግለሰቡ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ሳይንስ ሙዚየም፣ አድዋ ሙዚየም፣ ስላሴ ካቴደራል ቤተ ክርስቲያን ፣ በመስቀል አደባባይ እና ሌሎችም ቦታዎችን በመጎብኘት የዓለም ትኩረት ስቧል።

ዩቲዩበሩ በአዲስአበባ ጥሩ የሚባል አቀባበል ተደርጎለት እሱም እያመሰገነ ይገኛል። በኢትዮጵያ ቆይታዉ ብቻ ከ 250 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰብስክራይበሮችን ማግኘቱንም በመገረም ሲናገር ታይቷል።

ስፒድ በአዲስ አበባ ቆይታዉ በጥሩ መልኩ የኢትዮጵያን መልክ ለማሳየት የተደረጉ ጥረቶች መልካም የሚባሉ ነበሩ።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴርም አጋጣሚዉን በጥሩ የተጠቀመበት ሲሆን የወርቅ ብራስሌት፣ ጥሬ ስጋ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ማሰልጠኛ እና ሌሎች ታሪካዊ ሁነቶችን ተከታትሏል።

የቱሪዝም ሚንስትር ሰላማዊት እና በሚስወርልድ ውድድር ኢንተርናሽናል በ2025 በተካሄደው የቁንጅና ውድድር ላይ ሁለተኛ ሆና ካጠናቀቀችው ትንሳኤ ደረጀ ጋርም ቆይታ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ቡናን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀመሰዉ ስፒድ ጣዕሙን አድንቆ ለተከታዮቹ ሲናገርም ነበር።

የኢትዮጵያ ቆይታው ከ10 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን ያገኘ ሲሆን ይህም በአፍሪካ በታሪክ ከፍተኛው ሆኗል።

ከአዲስ አበባ ካይሮ የገባው ዩቲውበሩ በኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ እና ቦትስዋናን ጎብኝቷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *