ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ገለጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ጠይቀዋል፡፡

የፊፋ፣ ካፍ እና ሌሎች የእግር ኳስ አመራሮች በአዲስ አበባ በተካሄደው የካፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ላይ በተዘጋጀ እራት ግብዣ ላይ ንግግር ደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል።

የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል  ምስጋና አቅርበው፣ የኢትዮጵያውያን ባህል፣እሴትና እንግዳ ተቀባይነት ኢትዮጵያ  ቤታችን እንደሆነች እንዲሰማን አድርጎናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ ከኮሚቴው ጋር እንደሚመክርበት ገልዋጸል።

የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በበኩላቸው የሰው ዘር መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ የኛም  ሀገር ነች ሲሉ ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሁለቱም ፕሬዚዳንቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መለያን በስጦታ አበርክተዋል፡፡

በተመሳሳይ የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ 2029 የሚል ፊርማቸውን ያሳረፉበትን ኳስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አበርክተዋል።

ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታዎችን ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገዷል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ እስካሁን የካፍን ደረጃ ያሟላ ስታዲየም የሌላት ሲሆን ውድድሩን ለማዘጋጀት እያደረገች ስላለው ዝግጅት የተባለ ነገር የለም፡፡

ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች አንድ ስታዲየም ያላት ቢህንም ከዚህ ውስጥ አንዱም የካፍን ደረጃ የማያሟላ ሲሆን በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው እና 62 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ አልቻለም፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ብትሆንም እስካሁን ዋንጫውን አንድ ጊዜ ብቻ ማሸነፍ ችላለች፡፡

በ1962 የአፍሪካ ዋንጫን ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ተጫውታ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማሸነፍ ችላለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *