ወደ ቡዳፔስት አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ከነሀሴ 13 ቀን እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ሲካሄድ የቆየው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል።
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 195 የዓለማችን ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ሜዳሊያ ማግኘት የቻሉ ሀገራት ግን 46 ብቻ ናቸው ተብሏል።
ከማጣሪያ ውድድሮች ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ 2 ሺህ 100 አትሌቶች በተሳፉበት በዚህ ውድድር ላይ 50 አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ሲያስገኙ 48 የብር እንዲሁም 50 የነሀስ ሜዳሊያዎችን ተወዳዳሪዎቹ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡
ውድድሩን 400 ሺህ ተመልካቾች በአካል ስታዲየም ገብተው ታድመውታል የተባለ ሲሆን ሀንጋሪ ደማቅ እና አይረሴ ውድድር ማዘጋጀቷ ተገልጿል።
በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው ይህ ውድድር 52 አይነቶች የተካሄደ ሲሆን አሜሪካ በበላይነት አጠናቃለች።
አሜሪካ በዚህ ውድድር ላይ 12 ወርቅ 8 ብር እና 9 ነሀስ በድምሩ 29 ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች።
ውድድሩን በሜዳሊያ ብዛት በሁለተኝነት ያጠናቀቀችው ካናዳ በ4 ወርቅ በ2 ብር በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎችን ስትወስድ ስፔን ደግሞ በ4 ወርቅ እና በአንድ ብር በድምሩ በአምስት ሜዳሊያዎች ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች።
ጃማይካ በ3 ወርቅ፣ አምስት ብር እና አራት ነሀስ በምሩ በ12 ሜዳሊያዎች አራተኛ ስትሆን ጎረቤት ሀገር ኬንያ በ3 ወርቅ፣ ሶስት ብር እ ንዲሁም በአራት ነሀስ በድምሩ በ12 ሜዳሊያዎች ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ በአንደኝነት አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እንዲሁም በሶስት ነሀስ ሜዳሊዎች በድምሩ በ9 ሜዳሊያዎች ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ ሆና ማጠናቀ ቋን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረገጹ አስታውቋል።