በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች የረሀብ አድማ ጀመሩ

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

መንግሥትን በኃይል ለመጣል አሲረዋል በሚል የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ምሁራን የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ገለጹ።

ተጠርጣሪዎቹ የረሃብ አድማውን የጀመሩት ከትላንት ጀምሮ ሲሆን፤ አድማው ለሦስት ተከታታይ ቀን የሚቆይ እንንደሆነ ተገልጿል።

የረሃብ አድማው ላይ ከሚገኙት እስረኞች መካከል ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሳሳይ፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ እና ሌሎች የሽብር ክስ የቀረበባቸው ታሳሪዎች ይገኙበታል።

የአድማው ምክንያት ከእነሱ እስር በተጨማሪ በምንም ጉዳይ ላይ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች በብዛት የሚታሰሩበትን ሁኔታ ለመቃወም ነውም ተብሏል።

የፌደራል መንግሥት ጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ባወጣው መግለጫ፤ ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ማስታወቁ ይታወሳል።

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሲፒጂ በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ከህግ ውጪ እያሰረ እና እያንገላታ መሆኑን ገልጿል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የዜጎች መርጃን የማግኘት መብት በመንግስት ጫና ውስጥ ሙውደቁን ገልጾ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተጣለው ገደብ እንዲነሳ፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችም ከእስር እንዲለቀቁ አሳስቧል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *