የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደለ

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ መገደላቸው ተገለጸ።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል ተብሏል።

የአቶ ግርማን ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባወጡት የሀዘን መግለጫ አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀዘን መግለጫቸው ” ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም ” ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ” ሲሉም ገልጸዋል።

“ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። ” ሲሉም በድርጊቱ ማዘናቸውን ጽፈዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ በአማራ ክልል ከሚገኙ የወረዳ አመራርነት፣ የዞን አስተዳዳሪ እና እስከ ክልል ብልጽግና ሀላፊነት ድረስ አገልግለዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *