በሚዛን አማን ሁለት ህጻናት በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በኢትዮጵያ ሁለት ህጻናት በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

በመብረቅ አደጋ የአምስት እና የሰባት አመት እድሜ ያላቸዉ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት
ማለፉ ተገልጿል።

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በመብረቅ አደጋ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በከተማው አዲስ ከተማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ብርሃን አዲስ ከተማ ሠፈር ከቀኑ 8፡30 የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው መብረቅ የሁለት ህፃናት ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

አደጋው የደረሰው ሶስት ህጻናት ውሃ ለመቅዳት ወንዝ በሄዱበት ወቅት ዝናብ በመዝነቡ ለመጠለል ዛፍ ስር በሚገኝ ድንጋይ ላይ በተቀመጡበት ወቅት ነው።

በዚህ የመብረቅ አደጋ ምክንያትም የሁለቱ ህፃናት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።

የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች እየዘነበ መሆኑን ገልጾ በደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍ እና የመብረቅ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *