ጉምቱው ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ኢዜማን ለቀቁ

Andualem Arage

አቶ አንዷለም ኢዜማን ተሻጋሪ ለማድረግ የሰነቅነው ህልም ምላሽ ሊያስገኝልኝ አልቻለም በሚል እንደለቀቁ በማህበራዊ ትስስእ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መስራቾች አንዱ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ከፓርቲው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

አቶ አንዷለም ኢዜማን ከመጠንሰስ እስከ መመሥረት፣ ከምሥረታ በኋላም በአባልነት ፓርቲውን በአመራርነት አገልግለዋል።

አቶ አንዷለም ለፓርቲው ባስገቡት መግለጫ ላይ በፓርቲው ውስጥ የኢዜማ ስብራት ሲጠገን ለማየት አልቻልኩም ሲሉ ገልጸዋል።

በፓርቲው ውስጥ በሚያነሱት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል።

የፓርቲያችንን ቁመናና አሰላለፍ ከወዲሁ እናስተካክል የሚል ተማጽኖ ነበረኝ ያሉት አቶ አንዷለም ፓርቲው ይህንን እድል ሊፈጥር ባለመቻሉ መልቀቂያ ማስገባታቸውንም አክለዋል።

ኢዜማ በ2014 በተካሄደው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የግዢው ፓርቲ ሁነኛ ተፎካካሪ ነበር።

ምርጫው ከተጠናቀቀ እና ግዢው ፓርቲ ማሸነፉን ተከትሎ በፌደራ እና ክልል ተቋማት የሀላፊነት ሹመቶችን አግኝቷል።

የፓርቲው የተወሰኑ አመራሮች በገዢው ፓርቲ ሹመት መሰጠቱን ተከትሎ በኢዜማ አመራሮች እና አባላት መካከል መከፋፈል መፍጠሩ ከዚህ በፊት ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *