የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የበለጠ አጓጊ ሆኗል

የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሰናል ነጥብ ጣለ።

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ዌስትሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የአርሰናልን ግቦች ጋብሬል ጄሱስ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ሲያስቆጥሩ የዌስትሀምን የአቻነት ግቦች ቤንራህማ እና ጃርድ ቦውን አግብተዋል።

የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ በውድድር አመቱ አስራ አንደኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ከሜዳው ውጪ የተጫወተው አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ሰባ አራት ያደረሰ ሲሆን ቀሪ ጨዋታ ካለው ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ብሏል።

ዌስትሀም በበኩሉ በ31 ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የእንግሊዝ መርሀ ግብር አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ዌስትሀም ከ በርንማውዝ የሚገናኙ ይሆናል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ፉክክር በአጓጊነቱ ሲቀጥል ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ተፎካካሪነቱ ሲጨምር አርሰናል ደግሞ የበለጠ ጫና ውስጥ እየገባ ይገኛል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *