ኢትዮጵያዊው ወጣት በሚያምነው ፈረሱ ተገደለ

በደቡብ ኢትዮጵያ አንድ ወጣት ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት ፈረስ ህይወቱ አልፏል።

በደቡብ ክልል ጌድኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት የገዛ ፈረሱ የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

ወጣት ቅጤሳ አለሙ በጌድኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ ከሚኖርበት የገጠር ቀበሌ እንጨት ጭኖ ወደ ከተማ በማምጣት እንጨቱን ሸጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ ነበር።

ይህ የ26 ዓመት ወጣት ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ እያለ ፈረሱ በሞተር ብስክሌት ድምፅ ደንብሮ ወጣቱን መሬት ላይ ጥሎታል ተብሏል።

ወጣቱ ከፈረሱ አንገት ላይ የነበረ ረዥም ገመድ በወገቡ እንደመቀነት ታጥቆት ኖሮ  በርግጎ በሚሮጠዉ ፈረስ መሬት ለመሬት እየተጎተተ ከድንጋይና ከግንድ ጋር ይላተማል።

በአካባቢዉ ህብረተሰብ ትጋትና ርብርብ እንደምንም ፈረሱን ማስቆም ቢቻልም ወጣቱ በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ ማለፉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *