27
Feb
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት ስብሰባ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳልፏል። የአሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ኑሮ እና ተጠቃሚነት በመሠረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ሰፊ መሠረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሠራሮችን በመዘርጋት ሲሠራ መቆየቱን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውሷል። ባለፉት ዓመታት ውስጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የዕድገት ደረጃ መሠረት በርካታ ከተሞችን በመመሥረት ሰፋፊ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በተደረበት የዕድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ሕዝቡን እና ክልሉን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ሕገ-ወጥነትን…