ሕንዳዊው በኦሮሚያ ክልል አዳማ አካባቢ ህይወታቸው አልፎ ተገኙ

ህንዳዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ መገኘቱን በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል።

ህንዳዊ ዜግነት ያለው እና በአዳማ አከባቢ ቢሮውን ባደረገው በካልፓታሩ ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተሰኘ ተቋም (KPIL) ሲሰራ የነበረ ግለሰብ በአዳማ አከባቢ ሞቶ መገኘቱን በኢትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል።

ኤምባሲው ባወጣው አጭር መግለጫ ናቭ ሱቫሪዮ የተሰኙትና በአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ላይ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰብ፥ ” አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ የተገኘ ሲሆን የሞቱን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው ” ሲል አስታውቋል።

ሕንዳዊው አሟሟታቸው እስካሁን በይፋ ያልተገለጸ ሲሆን ተገድለው ይሁን በህመም እንደሞቱ ምርመራው እንደቀጠለ ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልልም ሆነ የጌደራል ፖሊስ እስካሁን ስለ ሕንዳዊው አሟሟት መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ከዚህ በፊት ቻንይናዊያን ዜጎች በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው እና ተገድለዋል መባሉ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *