New admin

1105 Posts
ምስሉ በጅማ ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ግለሰብ አመራር ቤት ውስጥ የተገኘን የጦር መሳርያ አያሳይም

ምስሉ በጅማ ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ግለሰብ አመራር ቤት ውስጥ የተገኘን የጦር መሳርያ አያሳይም

የመጀመርያው ምስል የተለያዩ ጠመንጃዎችን የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ምስል የጥይት እና የጦር መሳርያ ምስሎችን ያሳያል። ሶስተኛው ምስል ደግሞ የጦር መሳርያ የተገኘበትን ግለሰብ ምስል ያሳያል በማለት አጋርቶት ነበር።  ከዚህም በተጨማሪ  ይህ የፌስቡክ ፖስት በምስሉ ላይ የተመለከተው ግለሰብ “በጅማ የማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ሰብሳቢ እና የደብተራ መድሃንያለም ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ነው።” የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አብሮ አያይዟል። ይህ የፌስቡክ ፖስት በብዙ ስዎች ዘንድ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን ከ400 በላይ ግብረ መልሶችን ማግኘት ችሏል።  ይሁን እንጂ ምስሎቹ የቆዩ ሲሆኑ በፌስቡክ ገፁ የቀረበውን መረጃ እንደማይደግፉ ሀቅቼክ ማረጋገጥ ችሏል። በዚህም ምክንያት ሀቅቼክ መረጃውን ሀሰት ብሎታል።     በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ…
Read More
ምስሉ በአቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

ምስሉ በአቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ የተገኘ የጦር መሳርያን አያሳይም

በጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የትዊተር አካውንት ህገወጥ የጦር መሳርያዎች እና ጥይቶች በባህር ዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የፓትርያርኩ ፅ/ቤት አመራር በሆኑት በአቶ አቡነ አብርሃም መኖርያ ቤት ውስጥ ተገኝተዋል በማለት ሶስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ይህ የትዊተር ፖስት በፖሊስ ፍተሻ ከአቡነ አብርሃም የመኖርያ ቤት ውስጥ አምስት ክላሽንኮቭ መሳርያዎች ከ235 ጥይት ጋር ተገኝቷል የሚል የመግለጫ ፅሁፍን አጋርቶ ነበር።   ይህ ፅሁፍ ለንባብ እስከበቃበት ጊዜ ድረስ ይህ የትዊተር ፖስት ወደ አንድ መቶ ያህል ጊዜ መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተመልክተውታል። ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን ተመልክቶ መረጃውን እንደማይደግፍ በማረጋገጥ ሀሰት ብሎታል።  በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት ከቤተክርስትያኗ ሲኖዶስ እውቅና ውጭ የተለያዩ ጳጳሳትን…
Read More
ምስሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ አያሳይም

ምስሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ አያሳይም

የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኦሮሚያ እና የሶማልያ ክልል አካባቢዎች ላይ ከባድ ድርቅ መከሰቱን ያሳያሉ። ይህ ድርቅ በእነዚህ አካባቢዎች ለአምስት ተከታታይ አመታት ተከስቷል። ይሁን እንጂ በነዚህ አካባቢዎች ከተከሰቱት ድርቆች መካከል በቦረና የተከሰትው ድርቅ ከባዱ ነው። በምስራቃዊ እና ደቡባዊ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በተለይም የቦረና አካባቢ ባለፉት አመታቶች ከባድ በሆነ ድርቅ የተጎዳ አካባቢ ነው። ከዚህ ድርቅ ጋር በተያያዘ በባለፈው አመት በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ፤ ሴቶች እና አረጋውያን በምግብ እጥረት እና በድርቁ ምክንያት የቀንድ ከብቶቻቸውን በማጣታቸው ምክንያት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው ነበር።  በአሁኑ ሰዓት በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከአየር ንብረት መለዋወጥ እንዲሁም እነዚህ አካባቢዎች  ዝናብ በማጣታቸው ምክንያት የተከሰተ ነው።  ይህ ድርቅ ወደ…
Read More
ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

ምስሎቹ ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸውን C-130 ሄርኩሊዝ የጦር አውሮፕላኖችን ያሳያል?

አንድ የፌስቡክ ፖስት ግንቦት 7 ፤ 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው C-130 ሄርኩሊዝ ጀቶች የሚል ፅሁፍን አያይዞ አምስት ምስሎችን አጋርቶ ነበር። ይህ የፌስቡክ ፖስትም ከ44 ጊዜ በላይ ሲጋራ ከ500 በላይ ግብረ መልሶችንም ማግኘት ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ ሀቅቼክ ምስሉን አጣርቶ መረጃውን በከፊል ሀሰት ብሎታል።  በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት እስካሁን ድረስ ያልተፈታ ችግር ሆኗል።  ከጥቂት ወራት በፊት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በሚል በፌደራሉ መንግስት የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት በህወሓት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ይህ ስምምነት ለሰላም ንግግር እና ግጭቱን ለማቆም ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገምቶ ነበር።  የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በህወሓት አመራር በሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መካከል የቀጥታ የስልክ ንግግር (ውይይት)…
Read More
ተመድ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለጸ

ተመድ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለጸ

ተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እርዳታ ጠባቂ ለሆኑ ኢትዮጵያውን ድጋፍ ለማድረግ ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል አለ። ጽህፈት ቤቱ በአውሮፓውያኑ 2022 በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተፈጥሯዊ አደጋዎች እና በግጭት ምክንያት አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል ብሏል። ኦቻ ለዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ባወጣው ‘የኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ ዕቅድ’ በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ድጋፍ ለማቅረብ 3.99 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። አስቸኳይ ዕርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች መካከል 4.6 ሚሊዮን የሚሆኑት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸው ተመላክቷል። በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአምስት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ከፍተኛ…
Read More
አቡነ ማትያስ ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትግራይ ተጓዙ

አቡነ ማትያስ ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትግራይ ተጓዙ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ በትግራይ ሲካሄድ የነበረው ጦርነት ከቆመ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀለ ገቡ። ፓትሪያርኩ ወደ ትግራይ ያቀኑት ከቀናት በፊት በሞት በተለዩት የመቀለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጻጻስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ዳግማዊ የሽኝት ሥነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው። አቡነ ማቲያስ ለሁለት ዓመት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ወደ ትግራይ ሲያመሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ፓትሪያርኩ በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ በይፋ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ሰላም እንዲወርድም በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። ነገር ግን በትግራይ ክልል ያሉ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በጦርነቱ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ባሉ ምዕመናን…
Read More
በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ሁለት ”የጦር ጄቶች እጅግ ዝቅ ብለዉ በረሩ፡፡

በአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ሁለት ”የጦር ጄቶች እጅግ ዝቅ ብለዉ በረሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እኩለ ቀን 6 ሰዓት አካባቢ ” ሁለት ተዋጊ የጦር ጄቶች ” ዝቅ ብለው መብረራቸውን አሻም ተመልክታለች፡፡ አሻም ጉዳዩን ለማጣራት የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነን አነጋግራለች፡፡ኮሎኔል ጌትነት ” የጦር ጄቶች ዝቅ ብለው መብረራቸውን ” አረጋግጠው፣ ” የጦር ጄቶቹ ዝቅ ብለው የበረሩት ልምምድ እየተደረገ ስለሆነ” ነው ብለዋል፡፡ ”በመጪው የአድዋ ድል በዓል ደግሞ የጦር ጄቶች በስፋት ትዕይንት እንደሚያሳዩ”ም ተገልጿል፡፡ የጦር ልምምዱ እስካሁን የተደረገው ብቻ ነው ወይስ ቀኑን ሙሉ ይቀጥላል” ስትል ላነሳችላቸው ጥያቄ ” ይህ ምስጢር ነው፤ ነገር ግን ሁሉም ሰላም ነው፡፡” ሲሉ መልሰዋል፡፡
Read More
አረብ ኢምሬት ለ273 ኢትዮጵያዊያን ስኮላርሺፕ ሰጠች

አረብ ኢምሬት ለ273 ኢትዮጵያዊያን ስኮላርሺፕ ሰጠች

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ…
Read More
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳለፈ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳለፈ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 3ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ ዓመት ስብሰባ በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ከተማዎች እንደ አዲስ እንዲደራጁ ውሳኔ አሳልፏል። የአሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ኑሮ እና ተጠቃሚነት በመሠረታዊነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ሰፊ መሠረት ያለው ልማት በማስመዝገብ የተለያዩ የልማት ስትራጂዎችን በማመንጨት ስትራቴጂዎቹን ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አደረጃጀቶችንና አሠራሮችን በመዘርጋት ሲሠራ መቆየቱን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውሷል። ባለፉት ዓመታት ውስጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የከተማ ልማት ለማካሄድ በከተመዎቹ የዕድገት ደረጃ መሠረት በርካታ ከተሞችን በመመሥረት ሰፋፊ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁን በተደረበት የዕድገት ደረጃ ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ በመሆን ሕዝቡን እና ክልሉን የሚመጥኑ ከተሞችን ለመፍጠር እንዲሁም ሕገ-ወጥነትን…
Read More
በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በሱሉልታ ከተማ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገናል አሉ።

በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተቋቋመዉ በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ቀርዮ የተሰኘዉ ነዋሪዎች ቤታቸዉ እየፈረሰባቸዉ እንደሆነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤታቸዉ ድንገት ስለሚፈርስባቸዉ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸዉን ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡ ቤቶቹ ያለምን ማስጠንቀቂያ ድንገት በሌሊት ጭምር እየፈረሱ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ “እቃችንን እንኳን ለማንሳት ጊዜ አልተሰጠንም” ብለዋል፡፡ ቤቶቹን ማፍረስ ብቻም ሳይሆን የቤት ክዳን ቆርቆሮና በር ጨምር እየተወሰደበናቸዉ እንደሆነም ሰምተናል፡፡አሁን ላይ ቤት የፈረሰባቸዉ ዜጎች ጊዚያዊ ማረፊያ አጥተዉ ሜዳ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ነዋሪዎቹ ፤ ግማሾቹም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተሰደዱ ነዉ ተብሏል፡፡ “ቤቶቹ ህገወጥ ሆነዉ ቢገኙ እንኳን እንድናፈረስና ለቀን እንድንወጣ ጊዜ መሰጠጥ ነበረበት” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ…
Read More