27
Oct
የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ፆታ የ2025 የዓመቱ የጎዳና ላይ ምርጥ አትሌት ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህም ኢትዮጵያ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻን በዓመቱ በሁለቱም ፆታ ምርጥ ብቃት ካሳዩ አምስት አትሌቶች መካከል ተብለው እጩ ሆነዋል። በሴቶቹ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና አግኔስ ንጌቲች፣ ለኔዘርላንድስ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን እና ከስፔናዊቷ ማሪያ ፔሬዝ ጋር ምርጥ አምስት ውስጥ መግባት ችላለች። በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ከብራዚላዊው አትሌት ካይኦ ቦንፊን፣ ካናዳዊው አትሌት ኢቫን ዱንፊ፣ ኬንያዊው አትሌት ሳባስቲያን ሳዌና ከታንዛኒያዊው አልፎንስ ሲምቡ ጋር ምርጥ አምስት መግባት ችሏል። በለንደን ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በውድድር ዓመቱ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ…