Stgeorgefootballclub

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለ31ኛ ጊዜ አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለ31ኛ ጊዜ አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘንድሮውን የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አንስቷል። ባህርዳር ከነማ ውድድሩን በሁለተኝነት አጠናቋል። የ2015 የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ64 ነጥብ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ባህርዳር ከነማ ደግሞ በ60 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን በ49 ነጥቦች የውድድር ዓመቱን አጠናቀዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ወይም ፈረሰኞቹ ፕሪምየር ሊጉን ለ31ኛ ጊዜ አሸናፊ ሆነዋል። የወራጅነት ደረጃዎች ላይ ደግሞ አርባምንጭ እግር ኳስ ክለብ በ34 ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ በ18 እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ15 ነጥቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ ወርደዋል። የኮኮብ ግብ አግቢነት ደረጃውን የቅዱስ ጊዮርጊሱ እስማኤል አጎሮ በ25 የውድድር ዓመቱ ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኖ አጠናቋል።
Read More