27
Mar
ፒያኖን በድንቅ ብቃት ስለሚጫወቱ “የፒያኖዋ እናት” የሚል ስያሜን ያገኙት እማሆይ ፅጌማርያም በ100 አመታቸው ነው ያረፉትእማሆይ ጽጌማርያም ከ150 በላይ የረቂቅ ሙዚቃ ድርሰቶችን የጻፉ ሲሆን፥ ሦስት አልበሞችን በሲዲ እና በሸክላ ላይ ማሳተማቸውም ይታወሳል በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ በ100 ዓመታቸው አርፈዋል።እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከአቶ ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ወይዘሮ ካሣዬ የለምቱ በ1915 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለዱት። እማሆይ ጽጌማርያም ገብሩ በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል። ከትምህርት መልስም በ19 አመታቸው ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 አመታቸው ምንኩስናን መቀበላቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያሳያል። ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።…