30
Nov
የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሄንሪ ኪሲንገር በመቶ አመታቸው አረፉ ታዋቂው ዲፕሎማት እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የውጭ ፖሊሲ አሳቢ በኮነቲከት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ትናንት ለሊት መሞታቸውን የአማካሪ ድርጅታቸው ኪሲንገር አሶሺየትስ በመግለጫው ገልጿል። በፈረንጆቹ በ1969 የፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ከመሆናቸው በፊት በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተው አለም አቀፍ ግንኙነቶችን አስተምረዋል። የፕሬዚዳንት ጄራልድ ፎርድ የመንግስት ፀሀፊም ሆነው አገልግለዋል። ጎበዝ ተደራዳሪ ተብለው የተወደሱ ሲሆን በ1970ዎቹ አሜሪካ ከሶቪየት ኅብረት ጋር ያለውን ግንኙነት እንድትሻሻል ኪስንገር ትልቅ ሚና ነበራቸው። አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ መንገድ ጠርገዋል። እ.ኤ.አ. በ 1973 ኪሲንገር የፓሪስ የሰላም ስምምነትን በማሳካታቸው ከዲፕሎማት ለዱክ ቶ…