08
Oct
የዓለም ባንክ ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ በቅርቡ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሚደረገው ውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ የመጫወቻ ሜዳ እንደገጠመውና ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ ይፋ አድርጓል። "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ" በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ሪፖርት፣ በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ውድድር በዝርዝር ይተነትናል። ሪፖርቱ እንደሚለው፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ሳፋሪኮም 850 ሚሊዮን ዶላር የፈቃድ ክፍያ ባለመክፈሉና በስድስት የገበያ ዘርፎች ላይ የበላይነት ያለው ተቋም (SMP) ሆኖ በመቆጠሩ ውድድሩ ፍትሃዊ አይደለም። ኢትዮ ቴሌኮም ከደንብ አስከባሪው ከተቀመጠው የመገናኛ ዋጋ (MTR) በታች የድምጽ ጥሪ ዋጋ በማቅረቡ፣ ሳፋሪኮም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረግ እያንዳንዱ ጥሪ ላይ ኪሳራ እንደሚያስተናግድ ሪፖርቱ ገልጿል (በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል)።…