24
Oct
የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚዋሰኑበት የሰሜን ሸዋ ዞን ስራ የሚገኙ ወረዳዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ደራ የተሰኘው ወረዳ ደግሞ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት አካባቢ ሲሆን በሶስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 300 ንጹሃን ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡ ኦነግ ሸኔ ከሶስት ዓመት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ መንግስት ይህን የሽብር ቡድን ለማጥፋት እርምጃ እየወሰድኩ ነው ቢልም ቡድኑ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል፡፡ አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የደራ ወረዳ ነዋሪ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንዳሉት "በሦስት ሳምንታ ውስጥ ከ300 በላይ ንጹሐን በሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል።" ያሉ ሲሆን፤ ይህ እርሳቸው ያላቸው ትክክለኛ መረጃ እንደሆነ በመግለጽ፤ የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል እርግጠኛ መሆናቸውን…