ኦርቶዶክስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳት እንዲሾሙ ወሰነች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳት እንዲሾሙ ወሰነች

ላለፉት አምስት ቀናት በደዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቋል። በጉባኤው የማጠቃለያ ፕሮግራም ችግር ባለባቸው እና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ  ውሳኔ አሳልፏል። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። አቡነ ጴጥሮስ አክለውም "የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል፣ ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል፣ በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ውሳኔ ተላልፏል" ብለዋል። "የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን ይህንን የሚያስፈጽምም 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል…
Read More