ስራፈጠራ

ዳሸን ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ሸለመ

ዳሸን ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ሸለመ

ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈው ያሸነፉ ተወዳዳሪዎችን ሸልሟል፡፡ ባንኩ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጌያለሁ ያለ ሲሆን ለአሸናፊዎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር እስከ100 ሺህ ብር ሸልሟል። በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከነደፋቸው ትልልቅ መርሃ ግብሮች አንዱ ይህ የስራ ፈጠራ ውድድር መሆኑን ጠቁመው በመርሃ ግብሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ስድስት ሺህ  ተወዳዳሪዎችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡ አቶ አስፋው ለውድድሩ አሸናፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉ ሲሆን ባንኩ ለወደፊት አብሯቸው እንደሚሰራና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም ቃል ገብተዋል፡፡ ለመጨረሻው ዙር የደረሱ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው የተለያየ መጠን ያለው ሽልማት ያገኙ…
Read More