ሰዋሰው

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሰዋሰው መተግበሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሰዋሰው መተግበሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

በእለቱ አብነት አጎናፍርን ጨምሮ የሁለት አርቲስቶች የአልበም ምርቃት፣ የክብር ስጦና እና የፊርማ ስነ ስርአትም ተከናውኗል። ሀገር በቀሉ የሙዚቃ አገልግሎት ሰጪው “ሰወሰው” መተግበሪያ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማው በሰዋሰው መተግበሪያ እና በሰዋሰው ዩትዩብ ቻናል በኩል የሚሰራጩ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን የቅጂ መብት ለማስከበር ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል ። ይህ ስምምነት የኪነ-ጥበብ ስራዎቹ ተደራሽነት ላይም ትርጉም ያለው ለውጥ እንደሚፈጥር ተገልጿል። የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ ዲጅታላይዝ በማድረግ በኩል አሻራውን በማሳረፍ ላይ የሚገኘው ሰዋሰው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በገባው ስምምነት ከነበሩት የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ ወደ 9107 አጭር ቁጥር A ወይም B ብሎ በመላክ እለታዊ እና ሳምንታዊ የክፍያ የደንበኝነት ጥቅሎችን በመግዛት ደንበኞች የሚፈልጉትን ሙዚቃ እንዲያገኙ ያስችላል።…
Read More