ምርጫቦርድ

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሕልውናዬን የሚያከስም በመሆኑ አልቀበለውም አለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰሞኑ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉዳይ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ቦርዱ ከዚህ በፊት ህወሓት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ምርጫ በማድረጉ፣ ወደ ትጥቅ ትግል እና አመጽ ተግባር ገብቷል በሚል ፓርቲው እንዲከስም ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ ህወሓት ለምርጫ ቦርድ ባስገባው ማመልከቻ ጦርነቱ በሰላም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ እና ከሽብርተኝነት መሰረዙን ተከትሎ  በምርጫ ቦርድ የተላለፈብኝ ውሳኔ ይነሳልኝ ሲል አመልክቶ ነበር፡፡ ምርጫ ቦርድም ከዚህ በፊት በህወሓት ላይ ያስተላለፍኩት ውሳኔን መቀልበስ የምችልበት ህጋዊ አሰራር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቶም ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎም ህወሓት ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር…
Read More