መነሻ ገፅ

የቻይና ኩባንያዎች ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል ፈጥረዋል ተባለ

የቻይና ኩባንያዎች ከ300 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል ፈጥረዋል ተባለ

ኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከሳበችው ውስጥ ግማሹ በቻይናዊን የተያዘ እንደሆነ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከቻይና ንግድ ምክር ቤት እና ከቻይና ኢምባሲ ጋር በአዲ አበባ ተወያይተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዚህ ጊዜ እንደገለጸው ባለፉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ ከተጀመሩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 50 በመቶ የሚሆኑት በቻይና ባለሀብቶች የለሙ ናቸው፡፡ ውይይቱ የቻይና ባለሀብቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ሲሆን ውይይቱ ለቻይና ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት አካባቢን ለመፍጠር እና ተጨማሪ ባለሀበቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡ አሁን ላይ ቻይና በኢትዮጵያ ከ 3 ሺህ 300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀከቶችን በማልማት ላይ ናት የተባለ ሲሆን ቻይና በኢትዮጵያ ከ325 ሺህ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድሎች ፈጥራለችም ተብሏል፡፡ ከሶስት ወራት በፊት…
Read More
ሐዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ክልል ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ምን ላይ ናቸው?

ሐዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ክልል ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ምን ላይ ናቸው?

ጾታዊ ጥቃት በሰዎች ላይ አካላዊ፣ ወሲባዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ችግሮችን የሚያስከትልና ጾታን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም የኃይል ድርጊት ነው፡፡ ፍቅርተ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን በምትኖርበት ከተማ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት ምን እንደሚመስል ለጠየቅናት ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥታናለች፡፡ “ጾታዊ ጥቃት በቅርብ ሰው፣ በምናውቀው ሰው ነው የሚፈጸመው፡፡ በከተማዋ እና አቅራቢያ ብዙ አይነት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳሉ ይሰማኛል” ብላለች፡፡ “ወደ አደባባይ ያልወጡ ብዙ የጾታ ጥቃት ወንጀሎች አሉ” የምትለው ፍቅርተ “በቅርቡ የ14 ዓመት ጓደኛዬ በአጎቷ ተደፍራለች፡፡ እናት እና አባቷ ለማህበራዊ ጉዳይ ከቤታቸው ሲሄዱ አጎቷ ጋር እንድትሆን ብለው በአደራ አስቀመጧት፡፡ ነገር ግን የተሻለ ደህንነት አለው ብለው ባስቀመጧት ቤት ያስቀመጧት ይህች የ14 ዓመት ታዳጊ አጎቷ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡…
Read More
በኢትዮጵያ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 80 ሺህ ዜጎች እንደሚፈናቀሉ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 80 ሺህ ዜጎች እንደሚፈናቀሉ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እየተደጋገሙ ሲሆን እስካሁን መኖሪያ ቤቶች ላይ የተወሰኑ ጉዳቶችን ከማድረስ የዘለለ ከባድ ጉዳት አላደረሱም፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ30 ጊዜ በላይ በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ አቅራቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ከ60 ዓመት በኋላ ከፍተኛ የጠባለ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሟል፡፡ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት እንደገለጸው ከሆነ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሟል፡፡ በዚህ አደጋ ምክንያት በአፋር ክልል ባሉ መኖሪያ ቤቶች እና የመንግስት ተቋማት ላይ አነስተኛ ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን ንዝረቱ አዲ አበባ ድረስ ተሰምቷል፡፡ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው ማስታወቂያ የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ 12 ቀበሌዎች 80 ሺህ ዜጎችን ሊፈጠር…
Read More
ኢትዮጵያ ከውጪ ንግድ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከውጪ ንግድ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግድ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ በተጠቀሱት ጊዜያት ውስጥ 480 ሺህ ቶን የተለያዩ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገራት በመላክ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደተገኘ ተገልጿል፡፡ የተገኘው ገቢ ካምናው ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር የ947 ሚሊየን ዶላር ብልጫ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ከተገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ግብርና 53 ነጥብ 25 በመቶ ድርሻ ሲይዝ ማዕድን 37 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ 5 ነጥብ 43 በመቶ እንዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች 4 ነጥብ 33 በመቶ ድርሻ ይዘዋል፡፡ ወርቅ፣ ቡና፣ ኤሌክትሪክ እና የጥራጥሬ ምርቶች በገቢም ሆነ በመጠን ከዕቅዳችው በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ምርቶች መሆናቸውን የሚስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡ ከተላኩ ምርቶች መካከል 150 ሺህ ቶን…
Read More
ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ከወራት በፊት በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀው “የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ” በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ያልተለመዱ እና አዳዲስ የጤና አገልግሎቶች ለዜጎች እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ ለአብነትም በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚለው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሰዎች ህይወታቸው ስለሚቋረጥበት ሁኔታም በአዋጁ ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረትም በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን እንዲቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የዚህ ስርዓት አተገባበር መመሪያን በቀጣይ የጤና ሚኒስቴር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ…
Read More
በኢትዮጵያ ባንድ ቀን ውስጥ ከ14 ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

በኢትዮጵያ ባንድ ቀን ውስጥ ከ14 ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እየተደጋገሙ ሲሆን እስካሁን መኖሪያ ቤቶች ላይ የተወሰኑ ጉዳቶችን ከማድረስ የዘለለ ከባድ ጉዳት አላደረሱም፡፡ አደጋው እያጋጠመ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ልዩ ስሙ ፈንታሌ አካባቢ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ በአዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ባለዉ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ምክንያት ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየለቀቁ ሲሆን እስካሁን ከ2,500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እስካሁን ከፍተኛው 5 በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። በአደጋው ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አክለውም በቀን ውስጥ እስከ…
Read More
ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

በሀዋሳ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ሙሽራውን ጨምሮ 74 ሰዎች ሞተዋል። በትናንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ74 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) እንዳሉት "አይሱዚው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል። ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ በአጠቃላይ የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ…
Read More
የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

ሚዲያው እንደገለጸው ከህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ጋር በተያያዘ መረጃ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ ጋዜጤኞቹ  በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል። በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ያለውን ህገወጥ የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሂደትና የጎንዮሽ ጉዳቶቹ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ዘገባ ለመስራት ወደ ስፍራው ያቀናው የጋዜጠኞች ቡድን በታጣቂዎች ታግተዋል ሲል ተገልጿል። ሶስት ባለሙያዎችን የያዘው የጋዜጠኞች ቡድኑ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ጥዋት 3 ሰዓት በአስገደ ወረዳ፣ መይሊ ከተባለው ስፍራ ወጣ ብሎ በሚገኘውን መንደር በታጣቂዎች ተይዘዋል ተብሏል። ጋዜጠኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት በቦታው ተገኝተው ስላለው ነገር ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃዎችን ሲያሰባስቡ የቆዩ ሲሆን በተለይም በመይሊ አካባቢ ማዕድናቱን ለማውጣት በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ የተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች እያደረሱት ያለውን ጉዳት በተመለከተ መረጃዎች…
Read More
ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስስ ሳትካተት ቀረች

ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስስ ሳትካተት ቀረች

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ልዑክ (አትሚስ) የስራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) እንዲተካው ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ምክር ቤቱ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ አልሸባብን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች ከቀናት በኋላ አዲሱን ተልዕኮ እንዲጀምሩ ፈቅዷል፡፡ ውሳኔውን ለማጸደቅ ትላንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ ላይ ከ15 አባል ሀገራት በ14ቱ ድጋፍ ያገኝ ሲሆን ለሰላም አስከባሪ ሀይሉ በሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ቅሬታ ያነሳቸው አሜሪካ በድምጸ ተአቅቦ ወጥታለች፡፡ ቀደም ሲል በጸደቀው የምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በሶማሊያ የሚሰማሩ የሰላም አስከባሪ ሀይሎችን 75 በመቶ ወጪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚሸፍን ይገልጻል፡፡  በምክር ቤቱ ድምጽ መስጠት የማይችሉት ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ…
Read More
በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አባል ማህበራት የሰራተኞች ጥያቄ ካልተመለሱ  ስራ የማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በመንግስት እንዲወሰንና ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው ከፍተኛ_ግብር እንዲቀንስ መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም ተብሏል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሰራተኞች ወደ ስራ ማቆም አድማና ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያመሩ እንደሚችሉ ማህበራቱ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ይወክላሉ ከሚባሉት አባላቱ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት አድርጎት በነበረው ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አባላቱ በሰራተኞች ጥቅም ዙሪያ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ማህበራቱ በመግለጫቸው እስካሁን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎቻችን በመንግስት ባለመመለሳቸው ከዚህ በኋላ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንገደዳለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ…
Read More