ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ሆኑ

የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ፆታ የ2025 የዓመቱ የጎዳና ላይ ምርጥ አትሌት ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻን በዓመቱ በሁለቱም ፆታ ምርጥ ብቃት ካሳዩ አምስት አትሌቶች መካከል ተብለው እጩ ሆነዋል።

በሴቶቹ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና አግኔስ ንጌቲች፣ ለኔዘርላንድስ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን እና ከስፔናዊቷ ማሪያ ፔሬዝ ጋር ምርጥ አምስት ውስጥ መግባት ችላለች።

በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ከብራዚላዊው አትሌት ካይኦ ቦንፊን፣ ካናዳዊው አትሌት ኢቫን ዱንፊ፣ ኬንያዊው አትሌት ሳባስቲያን ሳዌና ከታንዛኒያዊው አልፎንስ ሲምቡ ጋር ምርጥ አምስት መግባት ችሏል።

በለንደን ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በውድድር ዓመቱ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በተጨማሪም በሴቶች ብቻ (በሴት አሯሯጮች ብቻ) በተደረገው ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን በእጇ ያስገባችበት ዓመት ሆኖም አልፏል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበኩሉ በዓመቱ በ5 ኪሎ ሜትር 6ኛውን የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን በ10 ኪሎ ሜትርም ምርጥ ሰዓት ባለቤትም ነው።

ከእነዚህ እጩዎች መካከል የዓመቱ ምርጥ አትሌትን ለመምረጥ በዓለም አትሌቲክስ ማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች (በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስ) ገጾች ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ክፍት ሆኗል።

ድምፅ የመስጠት ሂደቱ የሚጠናቀቀው ከአንድ ሳምንት በኋላ ማለትም ጥቅምት 23 ቀን 2018 ሲሆን የውድድሩ አሸናፊ ደግኖ ይፋ የሚደረገው ኅዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነም ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *