አቶ አንዷለም አድማሴ ሳፋሪኮምን ተቀላቀሉ

የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞው ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አንዷለም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተቀላቅለዋል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንዳስታወቀው የቀድሞውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴን የውጭ ግንኙነት ሃላፊው ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።

አንዷለም የኩባንያው የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ኾነው የተሾሙት፣ የቀድሞው ሃላፊ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ሻወል ከኩባንያው ለቀው ቦይንግ ኩባንያን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ነው።

አንዷለም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ያቋቋሙትን አንድ አዲስ የቴሌኮም ኩባንያ በሃላፊነት በመምራት ላይ ነበሩ::

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቴሌኮም አገልግሎት ነሀሴ 2014 ዓ.ም ላይ በድሬዳዋ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡

ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለ50 በመቶ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት የመስጠት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኔትወርክ ማስፋፊያ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድቤያለሁ ብሏል፡፡

ተቋሙ አክሎም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችበተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ 5 ሺህ አዳዲስ የኔትወርክ ማማዎችን እንደሚተክልም አስታውቋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የኔትወርክ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ እየሰጠ መሆኑን ያሳወቀው ሳፋሪ ኮም ቀስ በቀስ የራሱን የኔትወርክ መስመሮች እየገነባ እንደሆነም ገልጿል፡፡

አሁን ላይ ድርጅቱ በ2 ሺህ 500 የኔትወርክ ማማዎች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው የሚለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 500 ያህሉ ራሴ የገነባኋቸው ናቸውም ብሏል፡፡

የሳፋሪኮም የቀድሞ ውጭ ግንኙነት ሃላፊ አምባሳደር ሔኖክ ዓለማችን ስመ ገናናው የአቪዬሽን ተቋም ቦይንግ ባሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል፡፡

ኩባንያው እንዳስታወቀው በፈረንሳይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል፡፡

ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክን የሾመው ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር የሚኖረውን የንግድ እና ሌሎች ግንኙነት እንዲያሳልጡለት መሆኑን ገልጿል፡፡

አምባሳደር ሔኖክ አዲስ አበባ ሆነው ስራቸውን ያከናውናሉ የተባለ ሲሆን በቦይንግ የመካከለኛው ምስራቅ፣ ቱርክ እና አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ኩልጂት ጋታ አውራ ጋር ይሰራሉ ተብሏል፡፡

ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን አምባሳደር ሔኖክ ደግሞ የኩባንያውን የአፍሪካ ስራዎች እንደሚመሩ አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *