የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ሶማሊያ መጓዛቸውን የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ከዘጠኝ ወር በፊት በአዲስ አበባ የወደብ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
ይህ ስምምነትን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የተበላሸ ሲሆን ሶማሊያ ከግብጽ እና ቱርክ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ ግንባታ መጀመሯን ተከትሎ የውሃ ድርሻዬ ነካል በሚል ቅሬታ ያላት ግብጽ ይህንን እድል በመጠቀም ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን እያደረገች ነው፡፡
ይህን ተከትሎም ግብጽ ከሶማሊያ ጋር ባደረገቻቸው ወታደራዊ ስምምነቶች አማካኝነት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሞቃዲሾ ልካለች፡፡
ን የተፈራረምክንያት ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው አካል ነው።ወታደሮቹ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ማለትም በጌዶ፣ በሂራን እና በባይ ባኮል ስፍራዎች ላይ እንደሚሰፍሩ እየተገለጸ ይገኛል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በካይሮ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት ተከትሎ c-130 የተባሉ ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በአደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፋቸውን የሶማሊያ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ግብጽ ወታደሮቿንና የጦር መሳሪያዎችን በሶማሊያ ያሰማራችው በቅርቡ በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የባህር በር የመግባቢያ ስምምነትን ተከትሎ በቀጠናው ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው።
በሶማሊያ የግብፅ ኃይል መገኘት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ላለው አለመግባባት እና በአፍሪካ ቀንድ ለሚኖረው ፍላጎቶች እንደ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ተደርጎ ይወሰዳል ሲል የፑትላንዱ ጋሮዌ ኦንላይን ዘግቧል።
የወታዳራዊ ትብብሩ እ.ኤ.አ 2025 የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (አትሚስን) ለመተካት በታቀደው በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ አውሶምን አካል መሆኑ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ ሶማሊያ ከግብጽ እና ቱርክ ጋር ያደረገቻቸው ወታደራዊ ስምምነቶች ኢትዮጵያን አያሰጋም? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሶማሊያ ከፈለገችው ሀገራት ጋር ማንኛውንም ስምምነቶች ማድረግ መብቷ ነው ብለዋል፡፡
“ሶማሊያ ሉዓላዊ ሀገር ናት፣ እንደ ሀገር ከፈለገችው ጋር ማንኛውንም አይነት ስምምነት መፉራረም ትችላለች። ከግብጽ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያን አያስጨንቅም” ሲሉም መናገራቸው አይዘነጋም።