አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት ከአለም አቀፉ አሚአ ፓወር ኩባንያ ጋር ተስማምታለች፡፡

ስምምነቱ በዱባይ ከአራት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ እና አሚአ ኩባንያ ሀላፊዎች መካከል ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ለሚገነባዉ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማልማት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ከተሰማራው እና መቀመጫዉን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ካደረገዉ ከአሚአ ፓወር ጋር ስምምነት አድርጓል።

በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት አመንጭቶ ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው።

በኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን ለማልማት እና ለማንቀሳቀስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት እና የትግበራ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወቀው ኩባንያው  ይህ የ620 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 1 ሺህ 400 ጌጋ ዋት ሰዓት ኃይል እንደሚያመነጭ ይጠበቃል ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበኩሉ የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቀጣይ ለሚተገበሩ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማሳያ መሆን እንደሚችል አስረድቷል።

ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በተደረገው ስምምት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ላይ መሰረት ላደረገ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ስትራቴጂዋ ተጨማሪ ግብዓት ይሆናል ተብሏል።

የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ፣ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ እንደሚያስችልና በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።

ኬንያ ካሳለፍነው ጥር እስከ ሰኔ በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ ከኢትዮጵያ 672 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደገዛች የኬንያው ዘ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል።

ኬንያ ዘንድሮ በተጠቀሱት ወራት ውስጥ ከኢትዮጵያ የገዛችው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ88 በመቶ ብልጫ እንዳለው አለው።

ኬንያ አንድ ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ የምትገዛው፣ በ8 ነጥብ 6 የአሜሪካ ሳንቲም ነው ሲሆን  ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ፍጆታ ላይ በየሦስት ወሩ 10 በመቶ ታሪፍ ለመጨመር በቅርቡ የወሰነች ሲኾን፣ ለኬንያ ኃይል የምትሸጥበትን ዋጋ እንደገና ለመከለስ ግን እስከ ከሦስት ዓመት በላይ መጠበቅ ይጠበቅባታል።

ኢትዮጵያ ለሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለሱዳን ጅቡቲ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል በመሸጥ ላይ ስትሆን ለተጨማሪ ሀገራትም ሀይል ለመሸጥ የአዋጭነት ጥናት በማካሄድ ላይ ትገኛለች፡፡

ኬንያ አንድ ኪሎ ዋት ሀይልን በ6 ነጥብ 5 የአሜሪካ ዶላር ሳንቲም ለመግዛት የተስማማች ሲሆን በ2027 አዲስ ታሪፍ ስምምነት ልትፈራረም እንደምትችልም ተገልጿል፡፡

ኬንያ ከኢትዮጵያ በምትገዛው የኤሌክትሪክ ሀይል እስከ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎቿ የሀይል ፍላጎት በመሸፈን ላይ ትገኛለችም ተብሏል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *