ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክተዋል።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክታለች።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካዊያን አገልግሎት የሰጡ ተቋማትን እና ግለሰቦችን የህይወት ዘመን ሽልማት ይሰጣል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 25 ዓመታት በአሜሪካ ለሚኖሩ ዜጎች በሰጠው አገልግሎት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል።
አየር መንገዱ ሽልማቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ “ሽልማቱ ለሰጠው አገልግሎት እውቅና የሰጠ ነው” ብሏል።
ፕሬዝዳንት ባይደን የፈረሙበት ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች በአትላንታ በተዘጋጀ መርሀግብር ላይ ተቀብለዋል ተብላል።
የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሽልማቱ ባለፉት ዓመታት ለሰጠው የአቪዬሽን አገልግሎት እውቅና ባለፈ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን እንዲያሰፋ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ በሳምንት 30 በረራዎችን ወደ አሜሪካ ዋና ዋና ከተሞች በረራዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
አየር መንገዱ ከሚበርባቸው ከተሞች መካከል ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ቺካጎ እና አትላንታ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በ2016 በጀት ዓመት ከ7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንዳገኘ የገለጸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚሁ ተመሳሳይ ዓመት 17 ሚሊዮን መንገደኞችንም እንዳስተናገደ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጠው መግለጫ በ2023/24 በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዳሉት ይህ ትርፍ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል።
ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ስራ አስፈጻሚው አክለው እንደገለጹት አየር መንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።
አየር መንገዱ ካስተናገዳቸው 17 ሚሊዮን መንገደኞች መካከል 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው።