አዲስ አበባ ዓለም-አቀፍ የቦክስ ውድድር ልታስተናግድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን፣ ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡

ፌዴሬሽኑ የቢሮውን መክፈት አስመልክቶ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር እንደሚዘጋክ ተገልጿል፡፡

ይህ አለም አቀፍ የቦክስ ውድድርን የአለም አቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይዘጋጃል ተብሏል፡፡

20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከሩሲያ፣ ሜክሲኮ፣ እንግሊዝ፣ ካዛኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡

ይህ ልዩ የቦክስ ውድድር ላይ የተሳተፉ ቦክሰኞች በአፍሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል የተባለ ሲሆን ውድድሩ በ10 ዘርች ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ይህ አለም-አቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ በርካታ ሚዲያዎች ከተለያዩ ሀገራት እንደሚመጡም ተገልጿል።

በአፍሪካ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር ተዘጋጅቶ የማያውቅ ሲሆን የአሁኑን ውድድር የምታስተናግደው ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለችም ተብሏል።

ስመ ጥርና ፕሮፌሽናል ቦክሰኞችን ውድድር ማንኛውም ስፖርት ወዳድ ተመልካች በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ውድድሩን ለመመልከት ቅድሚያ 1 ሺህ 500 ብር መክፈል ግዴታ ሲሆን ውድድሩን መመልከት የሚፈልጉ ሰዎች በኦንላየን መክፈል እንደሚችሉ የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ቦክስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ 50 ሀገራትን በአባልነት የያዘ ሲሆን በ1960 የተቋቋመ የቦክስ ስፖርትን ለማሳደግ በሚል የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *