የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል።

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል ለኢትዮጵያ የሚደረግ ድጋፍ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ እንዲሁም 6 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂ ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ስራ አስፍጻሚ ቦርድ በትናትናው እለት ለኢትዮጵያ የአራት ዓመት የ3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን ማጽቁ ይታወሳል።

የተቋሙ ቦርድ ትናንት ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል መሆኑንም አስታውቋል።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የስራ አስፍጻሚ ቦርድ ቦርድ ብድሩን ያጸደቀው የኢትዮጵያ መንግስት በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያ የውጪ ንግድን ለማሳደግ በሚል የብርን የመግዛት አቅም በ31 በመቶ ያዳከመች ሲሆን አሁን ላይ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር እየተመነዘረ ይገኛል፡፡

By New admin

One thought on “የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

  • I was just as engaged with your work as I was. The visual presentation is elegant, and the written material is excellent. Although it appears that you’re concerned about the possibility of presenting something potentially viewed as dubious, I believe you should be able to address this concern. You might be able to get this sorted out sooner rather than later by seeing to it that you put your best foot forward.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *