የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።

የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል።

ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው። 

በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።

ይሁን እንጂ የአርመንገዱ የእቃ ጭነት ገቢው ግን ቅናሽ አሳይቷል።

አየር መንገዱ 54 ሺህ ቶን በላይ ጭነት ማጓጓዙን ገልጿል። አየርመንገዱ ከእቃ ጭነት ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ8 በመቶ ቅናሽ ማሳነቱ ጠቅሷል።

ስራ አስፋጻሚው እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየርመንገድ 125 አውሮፕላኖችን እንዲመረቱ ማዘዙን ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በዚሁ በጀት ዓመት ስድስት ዓለም አቀፍ አዲስ በረራዎችን ሲጀምር ሶስት ደግሞ የአሀገር ውስጥ በረራዎችን አድርጓል፡፡

አዲስ ዓለም አቀፍ በረራዎች ከተደረገባቸው መካከል ጋትዊክ፣ እንግሊዝ፣ ማድሪድ፣ ባንጉይ፣ ፍሪታወን፣ ማውን ቦትስዋና እንዲሁም ካዛብላንካ ካርጎ አዲስ በረራ ጀምሯል፡፡

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከመስከረም ወር ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱ ይታወሳል፡፡

የኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀጣዩ መስከረም በኋላ ወደ አሥመራ እንዳይበር ማገዱን የሚያሳውቅ ማስታወቂያ አውጥቷል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አስመለክቱ በሰጠው መግለጫ፤ “የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሐምሌ 14 2016 ዓ.ም ወይም ከመስከረም 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል” ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ገልጿል።

አቶ መስፍን በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የጣለውን እገዳ መልሶ እንዲያጤነው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *