ኢትዮጵያ ለቴሌቪዥን ስርጭት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙንኬሽን ሳተላይት ባለመያዟ ምክንያት በዓመት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለች መሆኗ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለንብረቶች ማህበር በየዓመቱ የሳተላይት ስርጭት የምንከፍለው ዋጋ ጭማሪ አሳስቦናል በሚል ነበር መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጥያቄውን ተቀብሎ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮሳት እንዲገቡ ያደረገው፡፡

ስርጭታችሁን በኢትዮ ሳት በኩል ብታደርጉ በየዓመቱ ለሳተላይት የምትከፍሉት ክፍያ ይቀንስላችኋል በሚል ለቴሌቪዥን ባለንብረቶች ያሳውቃል፡፡

በዚህ መሰረትም 70ዎቹ ስርጭታቸውን በኢትዮሳት በኩል ያደረጉ ሲሆን ዓመታዊ ወጪያቸው ግን እንዳልቀነሰላቸው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ብሮድካስተሮች ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ወጪ ለመቀነስ ብለው ወደ ኢትዮሳት የገቡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በዓመት ለሳተላይት ስርጭት 7 ሚሊዮን ዶላር እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሄም ንጉሴ፤ የኢትዮ-ሳት አገልግሎት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ መቀነሱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት ለመሆን እየሰራች ስለመሆኑም ምክትል ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ፤ በኢትዮሳት አሁን ላይ ከ70 በላይ የኃይማኖት፣ የንግድ፣ የህዝብና ሌሎች የሀገር ውስጥ ቻናሎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

የኢትዮ ሳት አገልግሎትም 17 ሚሊዮን ቤቶች ላይ መድረሱን ገልጸው ይህም ከተደራሽነት አንጻር ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

የዓለም አቀፉ የሳተላይት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ (SES) የኢትዮጵያ ዳይሬክተርና የምስራቅ አፍሪካ የሽያጭ ሃላፊ መነን አገኘሁ፤ በኢትዮጵያ ከ18 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቲቪ ተጠቃሚዎች መካከል 17 ሚሊዮኑ በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2017 ከነበረው ቴሌቪዥን ተጠቃሚ አንጻር አሁን ላይ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የኢት-ሳት ተደራሽነትም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ከሚገኙ 136 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች መካከል 70 የሚሆኑት የሀገር ውስጥ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *