ኢትዮጵያ ከዓለም ከአይኤምኤፍ ጋር ያላትን ልዩነት መፍታት እንዳልቻለች ተገለጸ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋሸንግተን በተካሄደው የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናትም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት የጠየቀች ሲሆን ተቋሙ ግን ብድር ለኢትዮጵያ ከመስጠቱ በፊት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡

ከተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ኢትዮጵያ የብሯን የመግዛት አቅም እንድታዳክም የሚለው ሲሆን ይህ ጉዳይ እስካሁን አጨቃጫቂ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ኢትዮጵያ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ድርድር ሲያደርጉ ከአንድ ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን በየጊዜው ሳይስማሙ በመለያየት ላይ ናቸው፡፡

ከአንድ ወር በፊት የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ አዲ አበባ መጥተው ለ15 ቀናት የተደራደሩ ቢሆንም ውይይቱ ያለስምምነት ተጠናቋል፡፡

ኢትዮጵያ ከ11 ዓመት በፊት በዩሮ ቦንድ የገዛችውን አንድ ቢሊዮን ዩሮ መክፈል ባለመጀመሯ ምክንያት ከጋና እና ዛምቢያ በመቀጠል ብድር መክፈል የማይችሉ ሶስተኛዋ ሀገር መባሏ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የዩሮ ቦንድ ብድሩን መክፈል ያልጀመርነው በገንዘብ እጥረት ሳይሆን ሁሉንም አበዳሪዎቻችንን እኩል ማየት አለብን ብለን ስለምናምን ነው ስትል ምላሽ መስጠቷ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ 29 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ብድር ያለባት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሹ ከቻይና የተገኘ ሲሆን የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላት በመጠየቅ ለይ ትገኛለች፡፡

የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ከቻይና ውጪ ያሉ ሀገራ እና አበዳሪ ተቋማት የብድር መክፈያ ጊዜን እስካሁን ለማራዘም ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡

ኢትዮጵያ እና ዓለም ከሁለት ሳምንት በፊት ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ97 ቢሊዮን ብር እርዳታ እና ብድር ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዓለም ባንክ ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 850 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ በእርዳታ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት እና ለማከናወን በሚል በብድር መልኩ ከባንኩ እንደተሰጠ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

በእርዳታ ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ለገጠር አካባቢዎች የምግብ ዋስትና፣ የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ለመደገፍ፣ 82 ዶላሩ ደግሞ በከተማ አካባቢዎች ምግብ ዋስትና ስራዎችን ለማረጋገጥ ይውላል ተብሏል፡፡

እንዲሁም 340 ሚሊዮን ዶላሩ በቆላማ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ቀሪው 275 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ያሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

ጦርነት፣ ኮሮና ቫይረስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኑሮ ውድነት እና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየፈተኑ ያሉ ክስተቶች ሲሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ቢቆምም ሌላ ጦርነት በአማራ ክልል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *